Psalms 15

የእግዚአብሔር ቤተኛ

የዳዊት መዝሙር።

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል?
በተቀደሰው ኰረብታህስ ማን መኖር ይችላል?

2አካሄዱ ንጹሕ የሆነ፣
ጽድቅን የሚያደርግ፤
ከልቡ እውነትን የሚናገር፤
3በምላሱ የማይሸነግል፤
በባልንጀራው ላይ ክፉ የማይሠራ፤
ወዳጁን የማያማ፤
4ነውረኛ በፊቱ የተናቀ፤
እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ግን የሚያከብር፤
ዋጋ የሚያስከፍለውም ቢሆን፣
ቃለ መሐላውን የሚጠብቅ፤
5ገንዘቡን በዐራጣ የማያበድር፣
በንጹሓን ላይ ጕቦ የማይቀበል፤
እነዚህን የሚያደርግ፣
ከቶ አይናወጥም።
Copyright information for AmhNASV